Tech/Server switch 2016/am

This page is a translated version of the page Tech/Server switch 2016 and the translation is 100% complete.

ዊኪሚድያ ፋውንዴሽን በዳላስ ውስጥ አዲሱን የመረጃ ማዕከሉን ሙከራ ላይ ያውላል። ይህም አደጋ ቢከሰት እንኳን ዊኪፒድያ እና ሌሎች የዊኪሚድያ ዊኪዎች መስመር ላይ መቆየታቸውን ያረጋግጣል። ሁሉም ነገር መሥራቱን ለማረጋገጥ ፥ የዊኪሚድያ ቴክኖሎጂ ክፍል የታቀዱ ሙከራዎችን ማካሄድ አለበት። ይህም እነርሱ ከአንድ የመረጃ ማዕከል ወደ ሌላ የመረጃ ማዕከል ለውጥ ማድረግ መቻላቸውን የሚያሳይ ይሆናል። ይህንን ሙከራ ለማዘጋጀት እና ያልታሰቡ ችግሮች ሲደርሱ ችግሮችን ለመቅረፍ ብዙ ሠራተኞች ያስፈልጋሉ።

ሁሉንም ፍሰት ወደ አዲሱ የመረጃ ማዕከል የሚያዞሩት በእ.ኤ.አ ማክሰኞ ኤፕሪል 19 ይሆናል።
እ.ኤ.አ ማክሰኞ ኤፕሪል 21 ላይ ቀድሞ ወደነበረው የመረጃ ማዕከል ያዞሩታል።

ክፋቱ ግን በሚድያዊኪ የአሠራር ገደብ ምክንያት ሁሉም እርማቶች በነዚህ ሁለት ዝውውሮች መሃል መቆም አለባቸው። ለዚህ መቆራረጥ ይቅርታ እየጠየቅን ለወደፊቱ ይህንን ችግር ለመቀነስ እየሠራን መሆናችንን እንገልጻለን።

ሁሉንም ዊኪዎች ለአጭር ጊዜ ያህል ከማረም ውጪ ማንበብ ይችላሉ።

  • በእ.ኤ.አ ማክሰኞ ኤፕሪል 19 እና ሐሙስ ኤፕሪል 21 ላይ በኢትዮጵያ ሠዓት አቆጣጠር ከቀኑ 11:00 ሠዓት (14:00 UTC,16:00 CEST, 10:00 EDT, 07:00 PDT) ጀምሮ በግምት ከ15 እስከ 30 ደቂቃ ለሚሆን ጊዜ ጽሑፎችን ማረም አይችሉም።
  • በዚህ ጊዜያት ለማረም እና ለመቆጠብ ከሞከሩ የስህተት ማመልከቻ መልዕክት ያያሉ። በዚህ ደቂቃዎች ውስጥ ምንም እርማቶች እንደማይጠፉ ተስፋ እናደርጋለን ፥ ነገር ግን ይህንን ማረጋገጥ አንችልም። የስህተት ማመልከቻውን መልዕክት ካዩ ፥ እባክዎ ሁሉም ነገር እንደ በፊቱ እስከሚሠራ ድረስ ይጠብቁ። ከዚያ በኋላ እርማትዎን መቆጠብ ይችላሉ። ለማንኛውም ግን የለውጦችዎን ቅጂ እንዲይዙ እንመክራለን።

ሌሎች ተጽዕኖዎች:

  • የበስተጀርባ ሥራዎች ሊዘገዩና አንዳንዶቹ ደግሞ ሊሠረዙም ይችላሉ። ቀይ ማያያዣዎች እንደበፊቱ ወዲያውኑ አይሻሻሉም። ከሌላ ቦታ ጋር ቀደም ሲል የተያያዘ ጽሑፍ ከፈጠሩ ፥ ማያያዣው ከወትሮው ዘግየት በማለት ቀይ ሆኖ ይቆያል። ለረጅም ጊዜ የሚሠሩ ስክሪፕቶችም መቆም ይኖርባቸዋል።
  • በእ.ኤ.አ ኤፕሪል 18 ሣምንት ውስጥ የኮድ መቆም ይኖራል። ምንም አስፈላጊ ያልሆኑ ኮዶች ተግባር ላይ አይውሉም።

ይህ ሙከራ እንዲካሄድ በመጀመሪያ የታቀደው በእ.ኤ.አ ማርች 22 ላይ ነበር። እ.ኤ.አ ኤፕሪል 19 እና 21 አዲሶቹ ቀኖች ናቸው። ፕሮግራሙን በwikitech.wikimedia.org ላይ ማንበብ ይችላሉ። በዚያ ፕሮግራም ላይ ማናቸውም ለውጦች ይለጠፋሉ። ለዚህም ተጨማሪ ማስታወቂያዎች ይኖራሉ። እባክዎ ይህንን መረጃ ለማኅበረ-ሰብዎ ያጋሩ። /User:Whatamidoing (WMF) (talk)